Skip to main content

ግላዊነት በ Microsoft

የእርስዎ ውሂብ፣ የእርስዎን ተሞክሮዎች ማጎልበት፣ በእርስዎ ቁጥጥር የሚደረግባቸው።

እዚህ በ Microsoft የእኛ ተልዕኮ በፕላኔቷ ላይ ያለን እያንዳንዱን ግለሰብ እና እያንዳንዱን ድርጅት ይበልጥ ስኬታማ እንዲሆን ማድረግ ነው። እኛ ይህንን ብልሃት የተሞላ ክላውድ በመገንባት፣ ምርታማነትን እና የንግድ ስራ ሂደትን ዳግም በመፍጠር እና በኮምፒዩተር መስራትን ይበልጥ ግላዊ በማድረግ በማከናወን ላይ እንገኛለን። በዚህ ሁሉ የግላዊነትን ጊዜ የማይሽረው እሴትን እንደነበረ እናቆያለን እንዲሁም የእርስዎን ውሂብ ለመቆጣጠር ያልዎትን ችሎታ በመጠበቅ ላይ እንሰራለን።

ይህም ውሂብ እንዴት እና ለምን እንደሚሰበሰብ እና ጥቅም ላይ እንደሚውል ትርጉም ያላቸው ምርጫዎችን እንዲያደርጉ እርስዎ መቻልዎን በማረጋገጥ ላይ እና በእኛ ምርቶች እና አገልግሎቶች ላይ በሙሉ ለእርስዎ ትክክለኛ የሆኑትን ምርጫዎች እንዲያደርጉ የሚያስፈልግዎትን መረጃ ማግኘትዎን በማረጋገጥ ስራ ይጀምራል።

በስድስት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ቁልፍ የግላዊነት መርሆዎች ላይ በመመርኮዝ የእርስዎን አመኔታ ለማግኘት በየቀኑ በመስራት ላይ ነን፦

  • ቁጥጥር፦ ለመጠቀም ቀላል ከሆኑ መሳሪያዎች እና ግልጽ ምርጫዎች ጋር የእርስዎን ግላዊነት በእርስዎ ቁጥጥር ስር እንዲሆን እናደርጋለን።
  • ግልጽነት፦ ስለ ውሂብ አሰባሰብ እና አጠቃቀም በተመለከተ በመረጃ ላይ ተመርኩዘው ከውሳኔ ላይ መድረስ እንዲችሉ ግልጽ እንሆናለን።
  • ደኅንነት በጠንካራ መድን እና ምስጠራ በኩል እርስዎ ለእኛ በአደራ የሰጡንን ውሂብ ጥበቃ እናደርግለታለን።
  • ጠንካራ ሕጋዊ ጥበቃዎች፦ የእርስዎን ከባቢያዊ የግላዊነት ሕጎች እናከብራለን እንዲሁም እንደ መሰረታዊ ሰብዓዊ መብት ለእርስዎ ግላዊነት ሕጋዊ ጥበቃ እንዲደረግ እንታገላለን።
  • ምንም ይዘትን የተመረኮዘ ዒላማ አደራረግ አይኖርም፦ የእርስዎን ኢሜይል፣ ውይይት፣ ፋይሎች ወይም ሌላ የግል ይዘት ወደ እርስዎ ማስታወቂያዎችን ዒላማ ለማድረግ አንጠቀምም።
  • ጥቅሞች ለእርስዎ፦ ውሂብን በምንሰበስብ ጊዜ እርስዎን ለመጠቀም እና የእርስዎን ተሞክሮ የተሻለ እንዲሆን ለማድረግ እንጠቀምበታለን።

እነዚህ መርሆዎች የ Microsoft ን የግላዊነት አያያዝ መሰረታዊ መርሆዎችን ይመሰርታሉ እና የእኛን ምርቶች እና አገልግሎቶች የምንገነባበትን መንገድ መቅረጻቸውን ይቀጥላሉ። ለኢንተርፕራይዝ እና ቢዝነስ ደንበኞች፣ የእርስዎን ውሂብ እንዴት ጥበቃ እንደምናደርግለት ለማየት የ Microsoft የታመኑ ማዕከልMicrosoft Cloud ውስጥ ይፈትሹ።

በዚህ የድር ጣቢያ የተቀረው ክፍል ላይ ለእርስዎ ትክክለኛዎቹን ውሳኔዎች መወሰን እንዲችሉ ተጨማሪ መረጃ እና መቆጣጠሪያዎችን የሚሰጡ አገናኞችን ያገኛሉ። እንዲሁም በቀጣይነት ለመሻሻል በመስራት ላይ ነን፤ ስለዚህ በእኛ ምርቶች እና አገልግሎቶች ላይ ግላዊነትን በተመለከተ እርስዎ እንደሚጠብቁት የማይሰራ ነገር ሲያገኙ እባክዎ እኛ እንድናውቀው ያድርጉን


Microsoft ምን ዓይነት ውሂብ ይሰበስባል?

Microsoft እርስዎ ተጨማሪ ነገሮችን ለማድረግ እንዲችሉ ለማገዝ ውሂብ ይሰበስባል። ይህን ለማድረግ፣ የእኛን ሶፍትዌር፣ አገልግሎቶች፣ እና መሳሪያዎች ለማሰራት እና ለማሻሻል፣ ግላዊነት የተላበሱ ተሞክሮዎችን ለእርስዎ ለማቅረብ እንዲሁም እርስዎ ደህንነትዎ እንደተጠበቀ እንዲቆዩ ለማገዝ የምንሰበስበውን ውሂብ እንጠቀምበታለን። እኛ የምንሰበስበው ውሂብ በብዛት የተለመዱ ምድቦች መካከል የተወሰኑት እነዚህ ናቸው።

የድር አሰሳ አደራረግ እና የመስመር ላይ ፍለጋዎች

ድር ላይ እያሰሰች እና ፍለጋ እያደረገች ያለች ሴት

ለእርስዎ የተሻሉ የፍለጋ ውጤቶችን ለመስጠት እንደ አብዛኛዎቹ የፍለጋ ፕሮግራሞች ሁሉ፣ የእርስዎን የፍለጋ ታሪክ፣ እና ከሌሎች ሰዎች የተውጣጣውን ታሪክ እንጠቀማለን። የድር አሰሳ አደራረግን ለማፍጠን፣ እርስዎ መሄድ የሚፈልጉበትን አስቀድሞ ለመገመት እንዲቻል የ Microsoft ድር አሳሾች የአሰሳ አደራረግ ታሪክን ሊሰበስቡ እና ሊጠቀሙ ይችላሉ። Cortana በእርስዎ የአሰሳ አደራረግ እና የፍለጋ ታሪክ ላይ በመመርኮዝ ግላዊነት የተላበሱ ምክሮችን ልትሰጥ ትችላለች።

በግብረመልስ እና ዳያግኖስቲክ የክንውን አውዶች የአሰሳ ታሪክዎ እንዲሰበሰብ ወይም እንዳይሰበሰብ በእርስዎ የWindows ግላዊነት የክንውን አውዶች ውስጥ መምረጥ ይችላሉ። በተጨማሪ Cortana ወደ የእርስዎ የፍለጋ እና የአሰሳ አደራረግ ታሪክ መዳረሻ ይኑራት አይኑራት በCortana እና Microsoft Edge የክንውን አውዶች ውስጥ ማስተዳደር ይችላሉ።

እርስዎ የሚሄዱባቸው ቦታዎች

በአይስክሬም መሸጫ መደብር አጠገብ መኪና መንዳት

የመገኛ አካባቢ መረጃ እርስዎ ሊሄዱ ስለሚፈልጉባቸው ቦታዎች አቅጣጫዎችን ለእርስዎ ለመስጠት እና አሁን ስላሉበት ቦታ ተዛማጅነት ያለውን መረጃ ለእርስዎ ለማሳየት እንድንችል ያግዘናል። ለዚህ ሲባል፣ እርስዎ የሚሰጡዋቸውን መገኛ አካባቢዎች ወይም እንደ GPS ወይም IP አድራሻዎች የመሳሰሉ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ፈልገን ያገኘናቸውን መገኛ አካባቢዎች እንጠቀማለን።

መገኛ አካባቢን ፈልጎ ማግኘት በተጨማሪ ለእርስዎ ጥበቃ እንድናደርግ ያግዘናል። ለምሳሌ፦ ከቶኪዮ ሁልጊዜ በሚቻል መልኩ በመለያ የሚገቡ ከሆነ እና ድንገት ከለንደን በመለያ ቢገቡ በእርግጠኝነት እርስዎ ራስዎ መሆንዎን ለማረጋገጥ እንችላለን።

በክንውን አውዶች > ግላዊነት > መገኛ አካባቢ ውስጥ ለእርስዎ መሳሪያ የመገኛ አካባቢ አገልግሎቶችን ማብራት ወይም ማጥፋት ይችላሉ። ከዚህ ላይ ሆነው፣ የትኛዎቹ የMicrosoft Store መተግበሪያዎች ወደ የእርስዎ መገኛ አካባቢ መዳረሻ እንደሚኖራቸው እና በእርስዎ መሳሪያ ላይ የተከማቸውን የመገኛ አካባቢ ታሪክ ማስተዳደር እንደሚችሉ እርስዎ መምረጥ ይችላሉ።

ከእርስዎ የMicrosoft መለያ ጋር የተገናኘ የአካባቢ ውሂብ ለማየት እና ለማጽዳት፣ ወደ account.microsoft.com ይሂዱ።

በግል፣ እርስዎን ለመርዳት የሚያግዘን ውሂብ

በእግረኛ መንገድ ላይ ስልኩን የሚያይ ሰው

ትራፊክን ማስወገድ እንዲችሉ፣ የልደት ቀኖችን እንዲያስታውሱ፣ በእርስዎ እውቂያ ዝርዝር ውስጥ ትክክለኛውን “ሰላማዊት” የሚል ስም መጻፍ እንዲችሉ እና በአጠቃላይ ተጨማሪ ነገሮችን እርስዎ ማድረግ እንዲችሉ ለማገዝ፣ Cortana የእርስዎ ዝንባሌ ምን እንደሆነ፣ በእርስዎ የቀን መቁጠሪያ ውስጥ ምን እንዳለ፣ እና ከማን ጋር ነገሮችን ማድረግ እንደሚፈልጉ ለማወቅ ትፈልጋለች። ወደ የእርስዎ የቁልፍ ሰሌዳ መድረስ በማይፈልጉበት ጊዜ፣ እርስዎ የሚናገሩትን ለመተርጎም ወይም በሰነዶች እና በጽሑፍ መልዕክቶች ላይ ለመጻፍ እርስዎን ለማገዝ የእርስዎን ንግግር እና የእጅ ጽሑፍ አጣጣሎችን መጠቀም እንችላለን።

የእርስዎን የ Cortana ፍላጎቶችን እና ሌላ ውሂብን ያስተዳድሩ

የአካል ብቃት እና ጤና

በጎዳና ላይ ብስክሌት የሚነዳ ሰው

Microsoft Health፣ HealthVault እና እንደ Microsoft Band አይነት መሳሪያዎች የእርስዎን የጤና ውሂብ እንዲረዱት እና እንዲያስተዳድሩ ሊያግዙዎት ይችላሉ።

የእርስዎ ውሂብ እንደ የእርስዎ የልብ ምት እና ዕለታዊ የተደረጉ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን የመሰሉ የነባራዊው ዓለም ውሂብን ሊያካትት ይችላል። ያንን ውሂብ ለማከማቸት HealthVault ን ለመጠቀም ከመረጡ የእርስዎን የጤና ሪኮርዶች በተጨማሪ ሊያካትት ይችላል። HealthVault በተጨማሪ ከእርስዎ ጤና ተንከባካቢዎች ጋር የእርስዎን የጤና ሪኮርዶች እንዲጋሩ ያስችልዎታል።

ይበልጥ አስደሳች የሆኑ ማስታወቂያዎችን ለማሳየት የምንጠቀምበት ውሂብ

በመንገድ ላይ የምትሄድ ሴት

አንዳንድ የMicrosoft አገልግሎቶች በማስታወቂያ የሚደገፉ ናቸው። እርስዎ ፍላጎቱ ሊኖርዎት የሚችልባቸውን ማስታወቂያዎች ለማሳየት እንደ የእርስዎ መገኛ አካባቢ፣ የ Bing ድር ፍለጋዎች፣ እርስዎ የተመለከቱዋቸው የ Microsoft ወይም የማስታወቂያ አስነጋሪ የድር ገጾች፣ ስነ ሕዝብ መረጃዎች እና እርስዎ ተወዳጅ ያደረጉዋቸው ነገሮችን የመሳሰለ ውሂብን እንጠቀማለን። ማስታወቂያዎችን ወደ እርስዎ ዒላማ አድርጎ ለመላክ በኢሜይል፣ በውይይት፣ በቪዲዮ ጥሪዎች ወይም የድምጽ ኢሜይል ወይም በእርስዎ ሰነዶች፣ ፎቶዎች ወይም ሌላ የግል ፋይሎች ውስጥ እርስዎ የሚሉትን ነገር አንጠቀምም።

በእርስዎ ዝንባሌ ላይ በመመርኮዝ Microsoft ለእርስዎ ማስታወቂያዎችን ማሳየቱን ለማስቆም የእኛን የማስታወቂያ ማስነገር ስራ መቆጣጠሪያዎች መስመር ላይ ይጠቀሙ። እንዲህም ሆኖ ማስታወቂያዎችን ማየትዎን ሊቀጥሉ ይችላሉ፣ ነገር ግን እርስዎ እንደሚፈልጉዋቸው ዓይነቶች አይሆኑም።

በመለያ መግባት እና የክፍያ ውሂብ

ለጠጣው ቡና እየከፈለ ያለ ሰው

ለራስዎ የ Microsoft መለያ መመዝገብ እንደ ማከማቻ እና የቤተሰብ የክንውን አውዶች የመሳሰሉ የመስመር ላይ አገልግሎቶችን እንዲጠቀሙ ያስችልዎታል፣ እንዲሁም በመሳሪያዎች ላይ በሙሉ የእርስዎን የክንውን አውዶች በማመሳሰል ውስጥ እንዲያቆዩ ያግዝዎታል። ወደ የእርስዎ መለያ የመክፈያ ውሂብ በሚያክሉበት ጊዜ፣ በእርስዎ የ Windows 10 መሳሪያዎች ላይ መተግበሪዎችን፣ የደንበኝነት ምዝገባዎችን፣ ፊልሞችን፣ ቲቪ እና ጨዋታዎችን ማግኘት ቀላል ነው።

የእርስዎን የይለፍ ቃል ምስጢራዊ አድርጎ በማቆየት እና እንደ የእርስዎ ስልክ ቁጥር ወይም የኢሜይል አድራሻ የመሳሰሉ ተጨማሪ ትርፍ የደህንነት መረጃ በማከል የእርስዎን ፋይሎችን፣ ክሬዲት ካርዶች፣ የአሰሳ አደራረግ ታሪክ፣ እና የግአኛ አካባቢ መረጃን ይበልጥ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ተቀባይነት ያለው ማድረግ ይችላሉ።

የይለፍ ቃሎችን፣ የደህንነት መረጃን፣ እና የክፍያ አማራጮችን ለማዘመን፣ Microsoft መለያ የድር ጣቢያ የሚለውን ይጎብኙ።

ከመሳሪያ ዳሳሾች የሚመጣ መረጃ

ከተገናኙ መሳሪያዎች ጋር ሶፋ ላይ ቁጭ ያለ ሰው

ከማንኛውም ዘመናዊ መሳሪያ እርስዎ ሊጠብቁት እንደሚችሉት አብዛኛዎቹ የ Windows 10 ስልኮች፣ ጽላቶች እና ፒሲዎች ከዳሳሾች—መሳሪያው ዓለምን እንዲመረምር የሚያስችሉት መንገዶች ጋር አብረው ይመጣሉ። ይህም የእርስዎ ስልክ ማይክራፎን ወይም አክስሎሜትር፣ የእርስዎ ላፕቶፕ የጣት አሻራ ቃኚ፣ ውስጣዊ የ GPS ዳሳሽ እና ተጨማሪ ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ።

በ Windows 10 መሳሪያዎች ላይ መሳሪያው እና መተግበሪያዎች ምን ዓይነት የዳሳሽ ውሂብ ሊጠቀሙ እንደሚችሉ እርስዎ በ የክንውን አውዶች > ግላዊነት መቆጣጠር ይችላሉ።


Windows 10 እና የእርስዎ የመስመር ላይ አገልግሎቶች

Windows 10 ዓርማ
ላፕቶፕ የምትጥቀም ዴስክ ላይ ቁጭ ያለች ሴት

በWindows 10 በክላውድ የጎለበት አገልግሎት በመጠቀም፣ ውሂብ የእርስዎን ተሞክሮ በቀጣይነት እንድንጠብቅ እና እንድናሻሽል ያግዘናል። ለምሳሌ፦ እርስዎን መስመር ላይ ደህንነትዎ እንደተጠበቀ እንዲቆዩ ለማገዝ፣ ለሚታወቁ ማልዌሮች በራስሰር የ Windows 10 መሳሪያዎችን እንቃኛለን። የእርስዎ መሳሪያ በደህና ሁኔታ መስራቱን እንዲቀጥል በተጨማሪ የእርስዎ የ Windows 10 ስርዓት በምን መልኩ ስራውን እያከናወነ እንዳለ ለማወቅ በቀጣይት መረጃን ለመቀበል ቴሌሜትሪ እንጠቀማለን። ስለዚህ ከአንድ የተወሰነ የአታሚ አንጻፊ ጋር የሆነ ችግር እንዳለ ካወቅን፣ ያንን የመሰለ አታሚ ለሚጠቀሙ ሰዎች ብቻ ትክክለኛዎቹን አንጻፊዎች እንልክላቸዋለን።

ግላዊነት የተላበሱ አገልግሎቶችን እና ተሞክሮዎችን በ Windows 10 ውስጥ ለማቅረብ መረጃ እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል ለመቆጣጠር የሚያስችሉ በርካታ መቆጣጠሪያዎችን በተጨማሪ እንሰጥዎታለን። የእርስዎን የWindows 10 ግላዊነት የክንውን አውዶች ለሁሉም ነገር፣ ከመሰረታዊ ቴሌሜትሪ እስከ ግላዊነት የተላበሱ አገልግሎቶች ድረስ በማንኛውም ጊዜ ወደ የክንውን አውዶች > ግላዊነት > ግብረመልስ እና ዳያግኖስቲክስ በመሄድ ማስተካከል ይችላሉ።

እያንዳንዱ የእኛ ምርት የእርስዎን ተሞክሮ ግላዊነት ለማላበስ እንዴት ውሂብ እንደሚጠቀም ይወቁ።

Office Office አርማ

በማናቸውም የOffice መተግበሪያ ላይ ወደ ፋይል > አማራጮች > የታማኝነት ማዕከል በመሄድ የግላዊነት የክንውን አውዶችን ይመልከቱ።

በእምነት ማዕከል ውስጥ የክንውን አውዶች

Skype Skype አርማ

የእርስዎን መገለጫ Skype ውስጥ እና Skype.com ላይ ባሉ ሌሎች የግላዊነት የክንውን አውዶች አማካኝነት ማን ማየት እንደሚችል አርትዕ ያድርጉ።

Skype የክንውን አውዶች

OneDrive OneDrive አርማ

የእርስዎን ፋይሎች በOneDrive ላይ ማን ማየት እንደሚችል መቆጣጠር ይችላሉ።

የእርስዎን ፋይሎች ደህንነታቸው እንደተጠበቀ ለማቆየት የተሻሉ አሰራሮች

Xbox Xbox አርማ

የእርስዎን የXbox የግላዊነት የክንውን አውዶች በእርስዎ ኮንሶል ወይም Xbox.com ላይ ያስተካክሉ።

Xbox የግላዊነት የክንውን አውዶች

Bing Bing አርማ

ወደ Bing.com በመለያ በመግባት የፍለጋ ጥቆማዎችን ያጥፉ እንዲሁም ሌሎች የክንውን አውዶችን ያስተካክሉ።

Bing የግላዊነት የክንውን አውዶች

Cortana Cortana አርማ

Cortana ከእርስዎ መሳሪያ እና ሌሎች የ Microsoft አገልግሎቶች ማወቅ በምትችልበት ጊዜ የተሻለ ትሰራለች።

የCortana የክንውን አውዶች