Windows 10 እና የእርስዎ የመስመር ላይ አገልግሎቶች – Microsoft ግላዊነት

Windows 10 እና የመስመር ላይ አገልግሎቶችዎ

Windows እንደ ፋይሎችዎ እና በስራ ላይ የሚገኙ መተግበሪያዎች የመሳሰሉ መሰረታዊ ተግባሮች የሚደግፍ የሶፍትዌር ፕሮግራም ያለው የክወና ስርአት ሲሆን፣ እንደ አታሚ፣ ሞኒተር፣ የቁልፍ ሰሌዳ እና መዳፊት የመሳሰሉ ውጫዊ መሳሪያዎች ይጠቀማል። ድሮ፣ Windows መሳሪያዎ ላይ ብቻ የሚገኝ ሶፍትዌር ተደረጎ ነበር የሚወሰደው። አሁን ከ Windows 10 መምጣት ጋር ተያይዞ፣ አስፈላጊ የሆኑ የ Windows ክፍሎች ክላውድ ላይ ከመስመር ላይ አገልግሎቶች ጋር ቁርኝት ፈጥረው ይገኛሉ። ስለ Windows 10 እዚህ ላይ ተጨማሪ ይወቁ።

Windows ለእነዚህ ጠቀሜታዎች እንዴት እና ለምን መረጃ እንደሚልክ ይህ ጽሁፍ ተጨባጭ ምሳሌዎችን ይሰጣል፦ ለእርስዎ እንደ Outlook፣ OneDrive፣ Cortana፣ Skype፣ Bing እና Microsoft Store ለመሳሰሉ የመስመር ላይ አገልግሎቶች መዳረሻ ለመስጠት፣ በWindows ላይ የእርስዎን ተሞክሮዎች ግላዊነትን የተላበሱ ለማድረግ፣ ምርጫዎችዎን እና ፋይሎችዎን በሁሉም መሳሪያዎችዎ ላይ ተመሳስለው እንዲቀጥሉ ለማገዝ፣ መሳሪያዎ እንደዘመነ እንዲቀጥል ለማገዝ፣ እንዲሁም ቀጣይወቹ የWindows ባህሪዎች እርስዎን የሚያስደስቱ ማድረግ እንድንችል።

እንዴት Microsoft መረጃን እንደሚጠቀም የተሰጡትን ዝርዝሮች በሙሉ ለመረዳት፣ Microsoft የግላዊ መረጃ ጥበቃ ቃል። ያንብቡ። Windows ለእርስዎ ግላዊነት የክንውን አውዶች ጥሩ መቆጣጠርያ ያቀርባል።


መሳሪያዎን መጠቀም

Office products on Windows 10 with a keyboard and mouse

መሳሪያዎ ካሜራ፣ ማይክራፎን፣ የመገኛ አካባቢ አገልግሎቶች፣ መልዕክት መላላኪያ፣ የእውቂያ ዝርዝር፣ እና የቀን መቁጠሪያ የያዘ ሊሆን ይችላል—እነዚህም ዋናዎቹ የጽላት፣ የዘመናዊ ስልክ፣ ወይንም ፒሲ ባህሪዎች ናቸው። ማናቸውም እነዚህን ባህሪዎች የሚጠቀሙ የMicrosoft Store መተግበሪያዎች በMicrosoft Store ውስጥ በሚገኘው የመተግበሪያ ምርት ማብራሪያ ገጽ ላይ በግልጽ ማሳወቅ አለባቸው። በተጨማሪ ማንኛውም የግል ውሂብ መጠቀምን የሚገልጽ የግላዊነት መግለጫ የያዘ አገናኝ ማቅረብ አለባቸው። ከነዚህ መተግበሪያዎች እንደ ካሜራ፣ ማይክራፎን እና አቅጣጫ መጠቆሚያ ያላቸው የትኞቹ መሆናቸው ለማየት እና ለመቆጣጠር፣ ወደ የክንውን አውዶች > ግላዊነት የሚለው ይሂዱ።

ከሰዎች ጋር መልዕክት መለዋወጥ communicating with people

ከጓደኞችዎ፣ ቤተሰብዎ፣ እና የቢዝነስ አጋሮችዎ ጋር እንደ የጽሁፍ መልእክት (SMS, MMS, etc.) በመሳሰሉ ዘዴዎች የ Windows መሳሪያ ላይ ኮሚዩኒኬት ሲያደርጉ፣ ወደ መልእክት መቀበያ ሳጥንዎ የምናደርሰው፣ ለእርስዎ የምናሳየው፣ ለመልእክቱ ምላሽ እንዲሰጡ የምናስችልበት፣ እና እስከሚሰርዙት ድረስ የምናስቀምጥልዎ የመልእክትዎ ይዘት ማግኘት አለብን። ለእውነተኛ-ጊዜ ኮሚዩኒኬሽኖች፣ የስልክ ጥሪ ማድረጊያ መተግበሪያ ሊደውሉለት የሚፈልጉት አካል ስልክቁጥር ማወቅ ይኖርበታል።

ሌሎች ከእርስዎ ጋር ግንኙነት እንዲያደርጉ ለማድረግ፣ የተወሰኑ አገልግሎቶች ሰዎች የኢሜይል አድራሻዎ ወይንም የስልክ ቁጥርዎ ተጠቅመው እንዲፈልጉዎ ይፈቅዳሉ። ለምሳሌ፤ የእርስዎን የኢሜይል አድራሻ ወይም የስልክ ቁጥርዎን የሚያውቁ ሰዎች እርሰዎን Skype ላይ ለመፈለግ እና ከእነርሱ ጋር ግንኙነት እንዲኖርዎት ግብዣ ለመላክ ሊጠቀሙበት ይችላሉ።

መተግበሪያዎችን መግዛት buying apps

መተግበሪያዎችን እና ሌሎች ነገሮች ከMicrosoft Store ሲገዙ፣ ወደ ባንክ የምንልከው የመክፈያ መረጃዎን እንሰበስብና ክፍያዎን እንሰበስባለን። ይህ የመክፈያ መሳሪያውን ቁጥር (ለምሳሌ የክሬዲት ካርድ ቁጥር)፣ የሒሳቡ ባለቤት ሙሉ ስም፣ እና የደህንነት ኮድ ሊያጠቃልል ይችላል።

የልጆችዎን ደህንነት እንደተጠበቀ ማቆየት keeping your kids safer.

ልጆች መሳሪያዎቻቸው እና መስመር ላይ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ለመረዳት እና ገደብ ለማድረግ፣ አዋቂዎች እንደ የማያ ገጽ ጊዜ፣ የእንቅስቃሴ ሪፖርት አደራረግ፣ እና ሌሎች ነገሮች የመሳሰሉ የቤተሰብ የክንውን አውዶችን ለመጠቀም ሊመርጡ ይችላሉ። በቤተሰቡ ውስጥ ያሉ አዋቂ ሰዎች ሁለት ግብዓቶች አሉዋቸው፦ account.microsoft.com/family የእንቅስቃሴ ሪፖርት አደራረግን እና ሌሎች የክንውን አውዶችን ማብራት ወይም ማጥፋትን ጨምሮ የልጆችን እንቅስቃሴዎች ለማስተዳደር እና account.microsoft.com/privacy የልጃቸውን ውሂብ ለመመልከት እና ለማጽዳት።

መሄድ ወደሚፈልጉበት ቦታ እርስዎን መውሰድ Getting where you want to go

በአገር አቋራጭ ትልቅ መንገድ ላይ ባለ አደጋ ዙሪያ የተሻለ በጣም ፈጣን የሆነውን የጉዞ መስመር ለእርስዎ ለመጠቆም፣ የካርታ መተግበሪያው እርስዎ አሁን የሚገኙበት ቦታ ማወቅ ያስፈልገዋል። ስልክዎ ከጠፋብዎ፣ የWindows ስልክዎን በካርታው account.microsoft.com ላይ የኔን ስልክ ፈልግ የሚለውን በመጠቀም ሊያገኙት ይችላሉ። የመገኛ አካባቢ ፈቃዶች እና የክንውን አውዶች እንዴት እንደሚሰሩ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ አቅጣጫ ጠቋሚ አገልግሎት እና ግላዊነት ያንብቡ።

Cortana

Cortana on Windows 10

MSN ስፖርትስ መተግበሪያ ላይ ስለሚከታሉዋቸው የስፖርት ቡድኖች ሰበር ዜና ለማግኘት፣ የካርታ መተግበሪያ ላይ የተመለከቱት ተወዳች ቦታዎችዎ ላይ የተመሰረቱ ጥቆማዎች ለማግኘት፣ እንዲሁም የአየር በረራ እቅድዎ ላይ የተከሰተ ለውጥ በሚኖርበት ጊዜ ማንቂያ ለማግኘት፣ እና ሌሎች ነገሮች ለማግኘት Cortana ማብራት ይችላሉ። ከ Cortana ጋር ምን ያክል ውሂብ እንደሚያጋሩ ሙሉ በሙሉ የሚቆጣጠሩት እርስዎ ነውት። Cortana እርስዎ በ Microsoft መለያ ሲገቡ እና የእርስዎን ውሂብ ከእርስዎ መሳሪያ ላይ፣ ከ Microsoft እና እርስዎ ለማገናኘት ከመረጡዋቸው የሶስተኛ ወገን አገልግሎቶች እንድትጠቀም ሲፈቅዱላት የተሻለ ትሰራለች። ሆኖም ግን ወደ Cortana በመለያ ላለመግባት ወይም ተጨማሪ ውሂብን ላለማጋራት ቢመርጡ እንኳ አሁንም ድረስ ከ Cortana ጋር መወያየት እንዲሁም ድሩን እና የእርስዎን የ Windows መሳሪያ እንዲያስሱ እንድታግዝዎት ሊጠቀሙባት ይችላሉ። Cortana የምትገኘው በተወሰኑ አገሮች/ክልሎች ብቻ ሲሆን የተወሰኑ የ Cortana ባህሪያት በሁሉም ቦታ ላይገኙ ይችላሉ። ስለ Cortana የክንውን አውዶች ተጨማሪ ለማወቅ Cortana እና ግላዊነት ያንብቡ።

በጥያቄዎ መሰረት እገዛ ለእርስዎ መስጠት Giving you help when you ask

ድጋፍ እንሰጥዎ ዘንድ ከጠየቁን፣ መልሰን እንድንደውልልዎ ወይንም ኢሜይል እንድንልክልዎ ስምዎ፣ ስልክ ቁጥርዎ፣ ወይንም የኢሜይል አድራሻዎ ሊሰጡን ይችላሉ። በተጨማሪ ድጋፍ የሚሹበት ችግር መግለጽ አለብዎ፣ ይህ ምን አይነት መሳሪያ እንደሚጠቀሙ፣ የትኛው የ Windows እትም እንደሚጠቀሙ፣ እንዲሁም ሌሎች እርስዎን ሶፍትዌር የሚመለከቱ መረጃዎች፣ ሊገናኙበት እየሞከሩት የሚገኘው አታሚ፣ ወይንም ሌላ አስፈላጊ መረጃ ሊያጠቃልል ይችላል። መሳሪያዎ እንዲጠገንልዎ ከፈለጉ፣ ጠግነን መልሰን እንድንልክልዎ የሚኖሩበት ቦታ ማወቅ ይኖርብናል።

ሊወዱዋቸው የሚችሉዋቸው ነገሮች ማሳየት Showing you stuff you might like

እርስዎ ሊወዱዋቸው ይችላሉ ብለን ስለምናስባቸው ነገሮች እንነግሮታለን። ለምሳሌ፣ የእርስዎ የመስመር ላይ ሱቅ ጋሪ ላይ ስለቀሩ እቃዎች ኢሜይል በመላክ ልናስታውስዎ እንችላለን። በተጨማሪ በአንዳንድ አገልግሎቶች ውስጥ ማስታወቂያዎችንም የምናሳይ ሲሆን፣ እርስዎ ሳቢ ሆነው ያገኙዋቸው ማስታወቂያዎች ልናሳይዎ እንመርጣለን። በፍላጎት ላይ የተመረኮዘ ማስታወቂያ ማስነገርን በእኛ አገልግሎቶች ላይ እንድናሳይዎት የማይፈልጉ ከሆነ፣ choice.microsoft.com ላይ እባክዎ እኛ እንድናውቀው ያድርጉ እና የእርስዎን ፍላጎት እናከብራለን።

ለእርስዎ ምን አይነት ማስታወቂያዎች ማሳየት እንዳለብን ለመምረጥ በኢሜይል፣ በውይይት፣ በቪድዮ ጥሪዎች ወይም በድምጽ ጥሪዎች፣ ወይም በሰነዶችዎ፣ ፎቶዎችዎ ወይም ሌሎች ግላዊ ፋይሎችዎ ላይ የተናገሩዋቸው ነገሮች አንጠቀምም።

ግላዊነት የተላበሱ መዝገበ ቃላቶች ማዘጋጀት Personalized dictionaries

የእውነት የሚያግዝ የጽሑፍ አስተያየት እና በራስሰር ማስተካከያዎችን ለእርስዎ ለማቅረብ፣ የተየቧቸውን እና በእጅ የጻፏቸውን ቃላት በናሙናነት በመጠቀም ግላዊነት የተላበሰ መዝገበቃላትዎን አዘጋጅተናል።

የትየባ ውሂቡ የተየቧቸውን ቁምፊዎች እና ቃላት ናሙና፣ በጽሁፉ ላይ በእጅ ያደረጓቸውን ለውጦች፣ እንዲሁም መዝገበቃላትዎ ላይ ያከሏቸውን ቃላት ያጠቃልላል። ይህ የግል መዝገበ ቃላት በእርስዎ መሳሪያ ላይ ሊቆይ ይችላል ወይም የእርስዎን የክንውን አውዶች በማመሳሰል በበርካታ መሳሪያዎች ላይ ከአገልግሎት መስጭ ክልል ውጭ ለመጠቀም ሊመርጡ ይችላሉ። Cortana ን ካበሩ፣ ግላዊነት የተላበሱ ጥቆማ ሃሳቦችን መስጠት እንድትችል እሷን ለማገዝ ንግግር፣ በእጅ መጻፍ እና ውሂብ በተጨማሪ ከ Cortana ጋር ያጋራሉ። እነዚህን የክንውን አውዶች ለመለወጥ ወደ የክንውን አውዶች > ግላዊነት > ንግግር፣ በእጅ መጻፍ እና መተየብ ይሂዱ። ይህን ባህሪ እና የእርስዎን ግላዊነት በተመለከተ ለተጨማሪ መረጃ፣ ንግግር፣ በብዕር መጻፍ፣ ትየባ እና ግላዊነትን ይመልከቱ።

ሁሉንም መሳሪያዎች ላይ ማመሳሰል

One map on multiple devices

ሁሉንም መሳሪያዎችዎ እርስዎ በሚፈልጉት መንገድ በራስሰር ለማቀናበር፣ የMicrosoft መለያ በመጠቀም ወደ Windows መሳሪያ ይግቡ፣ ከዚያም በሁሉም መሳሪያዎች ላይ የክንውን አውዶች እንዲመሳሰሉ ይምረጡ። ከዛ በኋላ፣ አንድ መሳሪያ ላይ የሚቀኙ የክንውን አውዶችን ከቀየሩ፣ ይህንን ለውጥ ወደ ሌሎቹ እንዲመሳሰሉ የመረጡዋቸው መሳሪያዎች በ Microsoft መለያ አማካኝነት በመለያ ሲገቡ እናመሳስለዋለን።

ለምሳሌ፣ የመለያ ምስልዎን፣ የበስተጀርባ፣ እና የመዳፊት የክንውን አውዶችን፣ የእርስዎን Microsoft Store መተግበሪያዎች የክንውን አውዶች፣ ግላዊነት የተላበሰው መዝገበ ቃላትዎን፣ የድር አሳሽ ታሪክ እና ተወዳጆችዎን እናመሳስላለን። የድር አሰሳ አደራረግ እና ሌሎች የማመሳሰያ የክንውን አውዶች ለመቀየር ወደ የክንውን አውዶች > መለያዎች > የክንውን አውዶችዎን ያመሳስሉ የሚለው ይሂዱ።

ፋይሎችን ማከማቸት እና ይዘት መፍጠር

ፋይል ወደ OneDrive ከጫኑ፣ በማንኛውም ከበይነመረብ ጋር የተገናኘ መሳሪያ ላይ ያገኙታል። ይህ ተደራሽ ለማድረግ፣ ይህንን ፋይል ወደ ማከማቻ ለመላክ፣ ማከማቻው ላይ ለእርስዎ ለማሳየት፣ እንዲሁም ለእርስዎ መልሰው እንዲያወርዱት ዝግጁ ለማድረግ ይዘቱን መሰብሰብ ይኖርብናል።

Microsoft Edge ላይ ድረገጾች ላይ በቀለም (በእጅ ጽሑፍ) ወይንም ማስታወሻዎን በመተየብ፣ በመቁረጥ፣ በማስቀመጥ፣ ወይንም በማጋራት አጭር መግለጫ ማስቀመጥ ይችላሉ። በተጨማሪ የንባብ ዝርዝሮችን መፍጠር እና ማስተዳደር፣ እና ሁሉንም እዚህ ዝርዝሮች፣ ተወዳጆች፣ ውራጆች፣ እና ታሪክ አንድ ቦታ ላይ ማስቀመጥ ይችላሉ። ይህንን በቀጥታ የእኛ አገልግሎት ላይ ስለፈጠሩት ከሁሉም መሳሪያዎች ላይ ሊደርሱበት ይችላሉ።

Windows ን ማሻሻል

የትኞች አገልግሎቶች ጥሩ እየሰሩ እንደሆኑ እና የትኞች ማሻሻል እንደሚያስፈልጋቸው ለመወሰን፣ ሰዎች Windows እንዴት ይጠቀማሉ የሚለው ላይ ትኩረት እናደርጋለን። ደንበኞቻችንን ባጋጠሙዋቸው ችግሮች ላይ ትኩረት መስጠት፣ መንስኤው ማወቅ፣ ችግሩን በፍጥነት ማስተካከል እንችላለን። በተጨማሪም ግብዓቶቻችንን ሰዎች በብዛት የሚጠቀሙባቸውን ነገሮች ለማሳደግና ጥቅም ላይ ያልዋሉትን ደግሞ ለማሻሻል ከዚያም ሲያልፍ ከስራ ለማስወጣት ትኩረት ማድረግ እንችላለን። ይህ ውሂብ፣ የዳያግኖስቲክ እና የአጠቃቀም ውሂብ፣ ሰዎች በWindows በውጤታማነት እንዲጠቀሙበት ማገዝ እንችል ዘንድ አገልገሎቶቻችን ያሉባቸውን ክፍተቶች ለመረዳት ያግዘናል።

የመገኛ አካባቢ አገልግሎቶችን ለማብራት ሰዎች ሲመርጡ፣ ስለ የተንቀሳቃሽ ስልክ ማማዎች መገኛ አካባቢ እና የ Wi-Fi መዳረሻ ነጥቦች መረጃ በመሰብሰብ የእኛን መገኛ አካባቢ አገልግሎቶች እናሻሽላለን። ይህ መረጃ ግለሰቡን ወይም ከየትኛው መሳሪያ እንደተሰበሰበ ተለይቶ ሳይታወቅ በውሂብ ጎታ ውስጥ ይከማቻል።

ንግግር፣ በብዕር መጻፍ እና ትየባ አብርተው ከሆነ፣ የመዝገበቃላት እና የእጅ ጽሁፍ መለየትን Windows ለሚጠቀም ሰው በሙሉ ለማሻሻል የእርስዎን የትየባ እና የእጅ ጽሁፍ ናሙናዎች እንሰበስባለን። ያስገቡ ተጠቃሚዎችን ለይቶ አዋቂዎችን ጥበቃ እያደረግንላቸው የምርት ማሻሻያ መረጃን መጠቀም እንድንችል ለይቶ አዋቂዎችን ለማስወገድ እና ውሂቡን በትናንሽ፣ አልፎ አልፎ የተቆራረጡ ቁራጮች ከፋፍሎ ለማስቀመጥ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እናደርጋለን።

Windows በተጨማሪ የእኛ Windows Insider ፕሮግራም ላይ ለተመዘገቡ ሰዎች ምርቱ በእድገት ደረጃ ባለበት ወቅት ግብረመልስ እንዲሰጡን ለማድረግ ቅድመእይታ ይሰጣቸዋል። Windows እንዴት እንደሚጠቀሙበት በማጥናት፣ እና ግብረመልሳቸውን በማድመጥ፣ ብዙ ሰዎች እና ኩባንያዎች የሚደሰቱባቸው የተሻሉ ምርቶችን ልናመርት እንችላለን።

የእኛን Windows Insider Program ለመቀላቀል እና ለእኛ ግብረመልስ ለመስጠት ከፈለጉ፣ በሚከተለው ላይ መቀላቀል ይችላሉ Insider.windows.com።

የስርዓትዎን ደህንነት መጠበቅ Making your system safer

To fight malware and help protect your device, we created features and tools like Windows Defender Antivirus, Windows Defender SmartScreen, and the Malicious Software Removal Tool. ማልዌርን ለመከላከል እና መሳሪያዎን ለመጠበቅ እንዲያግዝ፣ እንደ Windows ተከላካይ ጸረቫይረስ፣ Windows ተከላካይ SmartScreen እና የጎጂ ሶፍትዌር ማስወገጃ መሳሪያ ያሉ መሳሪያዎችን እና ባህሪዎችን ፈጥረናል። ሌላ ፀረማልዌር ሶፍትዌር መሳሪያዎን በንቃት እየጠበቀ ካልሆነ፣ መሳሪያዎን ከማልዌር እና ሌላ ያልተፈለገ ሶፍትዌር ለመጠበቅ እንዲያግዝ Windows ተከላካይ ጸረቫይረስ በራስሰር ይበራል። Windows ተከላካይ ጸረቫይረስ የበራ ከሆነ፣ የመሳሪያዎን የመድህን ሁኔታ ይቆጣጠራል። ስለተጠረጠረው ማልዌር እና ሌላ የማይፈልግ ሶፍትዌር ለMicrosoft ለመላክ ሪፖርቶችን በራስሰር ያዘጋጃል። አንዳንዴ፣ ሪፖርቱ ማልዌር የያዙ ፋይሎችንም ሊያካትት ይችላል። የተጠቃሚ ውሂብ የመያዝ እድላቸው ዝቅተኛ የሆኑ ፍይሎች በራስሰር ይላካሉ። ነገር ግን፣ Windows ተከላካይ ጸረቫይረስ የእርስዎን የግል ይዘት የመያዝ እድል ያለው ሰነድ፣ የተመን ሉህ ወይም ሌላ አይነት ፋይል መላክ የሚፈልግ ከሆነ እርስዎ እንዲፈቅዱ ይጠየቃሉ። Windows ተከላካይ ጸረቫይረስ ሪፖርቶችን እና የሚጠረጠር ማልዌርን በራስሰር ለMicrosoft መላኩን ለማስቆም፣ ወደ Windows ተከላካይ መድህን ማዕከል > የቫይረስ እና የስጋት ጥበቃ > የቫይረስ እና የስጋት ጥበቃ የክንውን አውዶች > የራስሰር ናሙና ማስገባት ይሂዱ።

Windows ተከላካይ SmartScreen የወረዱ ፋይሎች እና የድር ይዘት በሚጠቀሙባቸው ጊዜ በመፈተሽ፣ እርስዎ ላይ ወይንም መሳሪያዎ ላይ ችግር ሊፈጥሩ የሚችሉ ማልዌሮች፣ ተንኮል አዘል የድር ጣቢያዎች፣ የማይፈልግ ሶፍትዌር እና ሌሎች ስጋቶች እንዲያጣሩ ያግዞታል።

Windows ተከላካይ SmartScreen አንድ ፋይል የማይታወቅ ወይም ደህንነቱ የማያስተማምን ሆኖ ካገኘው ማስጠንቀቂያ ያሳይዎታል።

መሳሪያዊች የሚታወቅ ማልዌር እንዳይኖርባቸው ለመፈተሸ እና ካለም ለማስወገድ፣ የአታላይ ሶፍትዌር አስወጋጅ መሳሪያው መሳሪያሆ ላይ እንደ አንድ የ Windows Update አካል በመሆን ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ ይሰራል። የማልዌር ፍተሻ በሚደረግበት ጊዜ፣ የተገኘውን ማልዌር የሚመለከት ውሂብ፣ ስህተቶችን እና ሌላ መሳሪያዎን የሚመለከት ውሂብ የያዘ ሪፖርት ወደ Microsoft በመላክ እነዚህን ስጋቶች የበለጠ እንድንታገላቸው ያግዛል።

የእርስዎን ስርዓት ወቅቱን እንደጠበቀ ማቆየት

Windows ሳያቋርጥ መስራቱን እንዲቀጥል፣ ከምርት ዝማኔዎች፣ ከመድህን ዝማኔዎች እና አዳዲስ ባህሪያት ጋር ወቅቱን እንደጠበቀ እንዲቀጥል እናደርገዋለን። ዝመናዎች መሳሪያዎ ላይ በሚገባ መስራት መቻላቸውን ለማረጋገጥ፣ መሳሪያዎ ምን መስራት እንደሚችል እና ምን ድራይቨሮች እና ሶፍትዌሮች እንደጫኑ ማወቅ አለብን። በተጨማሪ ዝማኔው ስኬታማ ስለመሆኑ እንፈትሻለን።

ችግሮችን ማስተካከል Fixing problems

እርስዎ የሚጠቀሙባቸው አገልግሎቶች የሆነ ችግር ካጋጠማቸው፣ Windows ችግሩን ዳያግኖስ ለማድረግ እና ለመፍታት የሚያግዙ መረጃዎች ይሰበስባል። ለምሳሌ፣ ችግሪ ሲከሰት፣ መሰረታዊ ሶፍትዌር እና የሀርድዌር መረጃ ልንሰበስብ እንችላለን፣ የሶፍትዌር ብቃት እና የተስማሚነት ችግሮችን ልናይ፣ እና/ወይንም መተግበሪያዎችን፣ ድራይቨሮችን፣ እና በተመሳሳይ ጊዜ እያስኬዱዋቸው የሚገኙ መሳሪያዎች፣ እንዲሁም የችግሩ አይነት እና ክብደት ልንመለከት እንችላለን። መፍትሄዎች ሲኖሩ፣ ችግር ለመፍታት ወይንም ዝማኔዎች ለመጫን የሚያስፈልጉ ቅደምተከተሎችን እናቀርባለን። አንዳንዴ፣ ሰዎች ሪፖርት ያደረጉዋቸው ስህተቶች በቀጣይ የሚለቀቁ መሳሪያዎች እና አገልግሎቱ ዝማኔዎች ላይ መፍትሄዎች እንድናጠቃልል በማድረግ በመጪው ጊዜ ሰዎች ለሚያጋጥሙዋቸው ችግች በመፍትሄነት ልንጠቀምባቸው እንችላለን።